Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 1:1

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሠላሳኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ በዐምስተኛው ቀን፣ በኮቦር ወንዝ አጠገብ በምርኮኞች መካከል ሳለሁ፣ ሰማያት ተከፈቱ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

39 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህም በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፤ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ዋጋህም እኔው ነኝ።”

እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።

በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።

የእስራኤልንም አምላክ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ብሩህ ሰማይ የጠራ የሰንፔር ወለል ነበር።

በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፣ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ፤

ንጉሥ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን ከፍ ባለና በከበረ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።

እናንተም፣ “እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያት አስነሥቶልናል” ትላላችሁ፤

በባቢሎናውያን ምድር በኮቦር ወንዝ አጠገብ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቡዝ ልጅ፣ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ በዚያ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ነበረች።

እኔም አየሁ፤ እነሆ ከኪሩቤል ራስ በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ፣ የሰንፔር ዙፋን የሚመስል ነገር ነበረ።

የአራቱም መልክ ይመሳሰል ነበር፤ እያንዳንዱም መንኰራኵር በመንኰራኵር ውስጥ ተሰክቶ የተሠራ ይመስል ነበር።

ኪሩቤልም ወደ ላይ ተነሡ፤ እነዚህም በኮቦር ወንዝ አጠገብ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።

እነዚህ በኮቦር ወንዝ አጠገብ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ፤ ኪሩቤልም እንደ ሆኑ አስተዋልሁ።

ፊታቸውም በኮቦር ወንዝ አጠገብ ካየኋቸው ጋራ ይመሳሰል ነበር፤ እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።

መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም መንፈስ በተሰጠው ራእይም በባቢሎን ምድር ወደ ነበሩት ምርኮኞች አመጣኝ። ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ወጥቶ ሄደ፤

ከዚያም በኮቦር ወንዝ አጠገብ በቴልአቢብ ወደሚኖሩት ምርኮኞች መጣሁ፣ በድንጋጤ ፈዝዤም ከእነርሱ ጋራ ሰባት ቀን በመካከላቸው ተቀመጥሁ።

እኔም ተነሥቼ ወደ ረባዳው ስፍራ ሄድሁ። በኮቦር ወንዝ አጠገብ ያየሁት ዐይነት ክብር፣ የእግዚአብሔር ክብር በዚያ ቆሞ ነበር፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ።

በራእይ እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ ከፍ ባለ ተራራ ላይ አኖረኝ፤ ከተራራውም በስተ ደቡብ፣ ከተማ የሚመስሉ ሕንጻዎች ነበሩ።

ያየሁትም ራእይ ከተማዪቱን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ ያየሁትን ራእይ የሚመስልና እንዲሁም በኮቦር ወንዝ ካየሁት ራእይ ጋራ የሚመሳሰል ነበር፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ።

እርሱም እጅ መሳይ ዘርግቶ የራስ ጠጕሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ እርሱም ቅናት የሚያነሣው ጣዖት ወደ ቆመበት፣ ወደ ውስጠኛው አደባባይ መግቢያ ወደ ሰሜን በር ወደ ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ራእይ ወሰደኝ።

ለነቢያት ተናገርሁ፤ ራእይንም አበዛሁላቸው፤ በእነርሱም በኩል በምሳሌ ተናገርሁ።”

“ከዚህም በኋላ፣ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤ ጕልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ።

እንዲህ አላቸው፤ “ቃሌን ስሙ፤ “የእግዚአብሔር ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር፣ በራእይ እገለጥለታለሁ፤ በሕልምም እናገረዋለሁ።

እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቍጠሩ።

ከተራራው በመውረድ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ፣ “የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም እንዳትናገሩ” ብሎ አዘዛቸው።

ኢየሱስም እንደ ተጠመቀ ከውሃው ወጣ፤ ወዲያውኑም ሰማይ ተከፍቶ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድበት አየ።

ከውሃው በሚወጣበትም ጊዜ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ በርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤

ሕዝቡ ሁሉ ከተጠመቀ በኋላ ኢየሱስም ተጠመቀ፤ እየጸለየም ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤

ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ ሕዝቡም እንደ መሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፦ የኤሊ ልጅ፣

ጨምሮም፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማይ ተከፍቶ፣ የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ” አለው።

ሰማይም ተከፍቶ አንድ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራት ማእዘን ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድ አየ።

አንድ ቀን፣ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ የእግዚአብሔር መልአክ በራእይ ወደ እርሱ መጥቶ፣ “ቆርኔሌዎስ ሆይ!” ሲለው በግልጽ አየ።

“እነሆ፤ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ።

በመመካት የሚገኝ ጥቅም ባይኖርም፣ መመካት ካስፈለገ ከጌታ ወደ ተቀበልሁት ራእይና መገለጥ አመራለሁ።

ከዚያም ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ አንድ ነጭ ፈረስ ነበረ፤ በፈረሱም ላይ፣ “ታማኝና እውነተኛ” የሚባል ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።

ከዚህ በኋላ እነሆ፤ በሰማይ የተከፈተ በር አየሁ፤ ቀደም ሲል እንደ መለከት ሲናገረኝ የሰማሁት ድምፅ፣ “ወደዚህ ና፤ ከዚህም በኋላ ሊሆን የሚገባውን ነገር አሳይሃለሁ” አለኝ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች