ደግሞም በግብጻውያን ሥር በባርነት ሆነው ያሰሙትን የእስራኤላውያንን የሥቃይ ድምፅ ሰምቻለሁ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ።
እግዚአብሔር ኖኅንና በመርከቧ ውስጥ ከርሱ ጋራ የነበሩትን የዱርና የቤት እንስሳት ሁሉ ዐሰበ፤ በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም ጐደለ።
ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም።
ኪዳኑን ለዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል።
ከብዙ ዓመት በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያንም በባርነት ከደረሰባቸው ግፍ የተነሣ ይጮኹ ነበር፤ ከባርነት ቀንበር ለመላቀቅ ያሰሙትም ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ደረሰ።
እግዚአብሔርም የጩኸታቸውን ሲቃ ሰማ፤ ከአብርሃም፣ ከይሥሐቅና ከያዕቆብ ጋራ የገባውንም ቃል ኪዳን ዐሰበ።
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ “በግብጽ አገር የሚኖሩትን የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ፤ ከአሠሪዎቻቸው ጭካኔ የተነሣ የሚያሰሙትንም ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ሥቃያቸውንም ተረድቻለሁ።
የግብጽ ንጉሥም፣ “እናንተ ሙሴና አሮን፤ ለምንድን ነው ሕዝቡን ሥራ የምታስፈቱት? በሉ እናንተም ወደየሥራችሁ ተመለሱ!”
በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤ በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ ተሸከማቸውም።
ምሕረቱን በማስታወስ፣ ብላቴናውን እስራኤልን ረድቷል፤
ይህንም ያደረገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየት፣ ቅዱስ ኪዳኑን ለማስታወስ፣