ስለ እስራኤላውያን ከግብጽ መውጣት፣ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ሙሴና አሮን ነበሩ።
ባሪያውን ሙሴን፣ የመረጠውንም አሮንን ላከ።
በሙሴና በአሮን እጅ፣ ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው።
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ከግብጽ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ስተዋልና ውረድ” አለው።
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “አንተና ከግብጽ ያወጣኸው ሕዝብህ ይህን ስፍራ ለቅቃችሁ ‘ለዘርህ እሰጣለሁ’ በማለት ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ተስፋ ወደ ገባሁላችሁ ምድር ሂዱ።
በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር ስለ እስራኤላውያንና ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ነገራቸው፤ እስራኤላውያንንም ከግብጽ እንዲያወጡ አዘዛቸው።
እግዚአብሔር “እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብጽ አውጡ” ብሎ የነገራቸው አሮንንና ሙሴን ነበር።
እግዚአብሔር ሙሴን በግብጽ በተናገረው ጊዜ፣
ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ። አሮን በትሩን በፈርዖንና በሹማምቱ ፊት ጣላት፤ እባብም ሆነች።
ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤ እንዲመሩህ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።
“ ‘ከዚያም ሙሴንና አሮንን ላክሁ፤ ባመጣሁት መቅሠፍት ግብጻውያንን አስጨንቄ፣ እናንተን ከዚያ አወጣኋችሁ።
ከዚያም ሳሙኤል ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፣ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ያወጣ እግዚአብሔር ነው።