የየቤተ ሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ። እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው።
የሌዊ ልጆች፦ ጌርሶን፣ ቀዓት እና ሜራሪ ናቸው።
የሮቤል ልጆች፦ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው።
የየቤተ ሰቡም አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፤ ይሽዒ፣ ኤሊኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤርምያ፣ ሆዳይዋ፣ ኢየድኤል፤ እነዚህ ጀግና ተዋጊዎች፣ የታወቁ ሰዎችና የየቤተ ሰባቸው አለቆች ነበሩ።
የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ።
የቶላ ወንዶች ልጆች፤ ኦዚ፣ ረፋያ፣ ይሪኤል፣ የሕማይ፣ ይብሣም፣ ሽሙኤል፤ እነዚህ የየቤተ ሰባቸው አለቆች ናቸው፤ በዳዊት ዘመነ መንግሥት ከቶላ ዘሮች፣ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩት የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበረ።
የቤላ ወንዶች ልጆች፤ ኤሴቦን፣ ኦዚ፣ ዑዝኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ዒሪ፤ በአጠቃላይ ዐምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤ በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው ሃያ ሁለት ሺሕ ሠላሳ አራት ተዋጊ ሰዎች ተመዝግበዋል።
በጌባዕ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤
በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር ስለ እስራኤላውያንና ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ነገራቸው፤ እስራኤላውያንንም ከግብጽ እንዲያወጡ አዘዛቸው።
የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ።
ከዚያም በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበረ ሰቡን በሙሉ በአንድነት ሰበሰቧቸው። የተሰበሰቡትም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረጋቸውን ተናገሩ፤
የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤ በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤
ሙሴ በየጐሣቸው መድቦ ለሮቤል ነገድ የሰጠው ርስት ይህ ነው፤
የሮቤል ነገድ ወሰን የዮርዳኖስ ወንዝ ነው። የሮቤል ነገድ በየጐሣቸው የወረሷቸው ከተሞችና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ፤
ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል የየነገዱ ጐሣ አባቶች የደለደሉላቸው፣ እስራኤላውያንም በከነዓን ምድር የወረሱት ርስት ይህ ነው።
እንግዲህ ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የየጐሣ መሪዎች ሴሎ ላይ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ፣ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ ያደላደሉት ርስት ይህ ነው፤ የምድሪቱንም አከፋፈል በዚህ ሁኔታ ፈጸሙ።