ከዚያም መጋረጃውን በማደሪያው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለው።
እግዚአብሔር እንዳዘዘውም መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣን አጠነበት።
የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ አኖረው፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን መሥዋዕት በላዩ ላይ አቀረበ።
የዕጣኑን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት አስቀምጠው፤ ከማደሪያውም መግቢያ ላይ መጋረጃውን አድርግ።
በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል፤ ይገባል፤ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።
ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ሁላችንም በርሱ አማካይነት በአንዱ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና።