Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘፀአት 40:24

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከጠረጴዛው ትይዩ ከማደሪያው ድንኳን በስተ ደቡብ በኩል አኖረው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።

ጠረጴዛውን ከመገናኛው ድንኳን በሰሜን በኩል ከመጋረጃው ውስጥ አስቀምጠው፤ መቅረዙንም ከርሱ ትይዩ በማድረግ በደቡብ በኩል አድርገው።

እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ኅብስቱን በላዩ ላይ በእግዚአብሔር ፊት አኖረ።

እግዚአብሔር እንዳዘዘውም መብራቶቹን በእግዚአብሔር ፊት አበራ።

ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አምጥተህ ዕቃዎቹን በላዩ ላይ አሰናዳ፤ ከዚያም መቅረዙን አስገብተህ መብራቶቹን በቦታቸው አስቀምጥ።

በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋራ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም።

ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጪ የሆነው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር።

ኢየሱስ እንደ ገና ለሰዎቹ፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።

በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።

እንግዲህ ከየት እንደ ወደቅህ ዐስብ፤ ንስሓ ገብተህ ቀድሞ ታደርገው የነበረውን ነገር አድርግ፤ ንስሓ ካልገባህ፣ መጥቼ መቅረዝህን ከቦታው እወስድብሃለሁ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች