የአደባባዩ መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋራ፣ የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ፤ ገመዶቹና የአደባባዩ ድንኳን ካስማዎች፤ የማደሪያው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች ሁሉ፤
የንሓስ መሠዊያው ከንሓስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ ሁሉ ጋራ፤ የመታጠቢያው ሳሕን ከነማስቀመጫው፤
በመቅደሱ ሲያገለግሉ የሚለበሱት የተፈተሉት ቀሚሶች፣ ለካህኑ ለአሮን የተቀደሱት ቀሚሶችና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚያደርጓቸው ቀሚሶች ናቸው።
“የድንኳንሽን ቦታ አስፊ፤ የድንኳንሽን መጋረጃዎች በትልቁ ዘርጊ፤ ፈጽሞ አትቈጥቢ፤ ገመዶችሽን አርዝሚአቸው፤ ካስማዎችሽንም ቀብቅቢ።