ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ከመጠምጠሚያው ጋራ ለማያያዝ ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።
“ከንጹሕ ወርቅ ዝርግ ሳሕን አበጅተህ፣ ቅዱስ ለእግዚአብሔር በማለት በማኅተም ላይ እንደሚቀረጽ ቅረጸው።
የሚሠሯቸው መጐናጸፊያዎች የደረት ልብስ ኤፉድ ቀሚስ፣ ጥልፍ ሸሚዝ፣ ጥምጥምና መታጠቂያ ናቸው፤ ካህን ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ የተቀደሱ መጐናጸፊያዎችን ለአሮንና ለወንድ ልጆቹ ይሠራሉ።
ከንጹሕ ወርቅ የተቀደሰውን አክሊል ሰሌዳ ሠርተው፣ በማኅተም ላይ እንደ ተቀረጸ ጽሑፍ፤ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የሚል ቀረጹበት።
በዚህ መሠረት የማደሪያው ድንኳን፣ የመገናኛው ድንኳን ሥራ በሙሉ ተጠናቀቀ። እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉን ነገር ሠሩ።
ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰበ።