ከዚያም ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ልክ ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ ከመጋጠሚያው አጠገብ፣ ከኤፉዱ ፊት ለፊት ካሉት ከትከሻ ንጣዮች ጋራ አያያዟቸው።
ዐምስቱን መጋረጃዎች አገጣጥመህ ስፋ፤ የቀሩትንም ዐምስት መጋረጃዎች እንደዚሁ አገጣጥመህ ስፋቸው።
በጥበብ የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር ከኤፉድ ጋራ አንድ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን።
ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከኤፉዱ ቀጥሎ ካሉት ከሌሎቹ ሁለት የደረት ኪስ ጐኖች ጋራ ከውስጠኛው ጠርዝ ላይ አያያዟቸው።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ተነጥሎ ለብቻው እንዳይንጠለጠል የደረት ኪሱን ቀለበቶች ከመታጠቂያው ጋራ በማገናኘት፣ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋራ በሰማያዊ ፈትል አሰሯቸው።