ከመወዝወዙ ስጦታ የሆነው ናስ ሰባ መክሊትና ሁለት ሺሕ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።
አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰባ ዐምስት ሰቅሎችን ለምሰሶዎቹ ኵላቦች፣ የምሰሶዎቹን ዐናት ለመለበጥና ዘንጎቻቸውንም ለመሥራት አገልግሎት ላይ ውለው ነበር።
ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ ለናስ መሠዊያው ከናስ መጫሪያው፣ ለዕቃዎቹም ሁሉ መቆሚያዎቹን ለመሥራት አገልግሎት ላይ አውለውት ነበር፤