አንዱን ኪሩብ በአንዱ ጫፍ ላይ፣ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ጫፍ ላይ ሠራ፤ ከሁለቱ ጫፎች ላይ ከክዳኑ ጋራ አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው፤
ከዚያም ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሁለት ኪሩቤልን በስርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ ሠራ።
ኪሩቤልም የስርየት ክዳኑን በመሸፈን ክንፋቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ነበር፤ ኪሩቤል ወደ ስርየት መክደኛው እየተመለከቱ እርስ በርሳቸው ገጽ ለገጽ ነበሩ።