ድንኳኑን አንድ ወጥ አድርጎ ለማያያዝም ዐምሳ የንሓስ ማያያዣዎችን ሠሩ።
ከዚያም የመገናኛው ድንኳን አንድ ወጥ ይሆን ዘንድ መጋረጃዎቹን በአንድ ላይ ለማያያዝ ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሥራ።
በስተመጨረሻ በሚገኘው መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ በሌላ በኩል ባለው በስተመጨረሻ በሚገኘው መጋረጃ ጠርዝ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጁ።
ከዚያም ለድንኳኑ መሸፈኛ የሚሆን ቀይ ከተነከረ የአውራ በግ ቈዳ ሠሩ፤ በላዩ ላይ የሚሆንም የአቆስጣ ቈዳ አበጁ።
“ማደሪያውን ይኸውም የመገናኛውን ድንኳን በወሩ የመጀመሪያ ቀን ትከለው፤