ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ በማጋጠም ሰፏቸው፤ የቀሩትን ዐምስቱንም እንዲሁ አደረጉ።
ኢየሩሳሌም እጅግ እንደ ተጠጋጋች፣ ከተማ ሆና ተሠርታለች።
ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!
ዐምስቱን መጋረጃዎች አገጣጥመህ ስፋ፤ የቀሩትንም ዐምስት መጋረጃዎች እንደዚሁ አገጣጥመህ ስፋቸው።
ተጋጥሞ ከተሰፋው መጋረጃ ጠርዝ ጫፍ ላይ ከሰማያዊ ግምጃ ቀለበቶችን አበጁ፤ ተጋጥሞ በተሰፋው በሌላው መጋረጃ ጫፍ ላይም ተመሳሳይ ነገር አደረጉ።
መጋረጃዎቹም ሁሉ ተመሳሳይ መጠን ያላቸው ሲሆን፣ ቁመታቸው ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዳቸው አራት ክንድ ነበር።
“በዚያ ጊዜ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም እንዲጠሩ፣ ተስማምተው እንዲያገለግሉት፣ አንደበታቸውን አጠራለሁ።
የበዓለ ዐምሳ ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድነት፣ በአንድ ስፍራ ተሰብስበው ነበር።
ወንድሞች ሆይ፤ በመካከላችሁ መለያየት እንዳይኖር፣ አንድ ልብ፣ አንድ ሐሳብ እንዲኖራችሁ፣ እርስ በርሳችሁም እንድትስማሙ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።
እንግዲህ ብልቶች ብዙ ናቸው፣ አካል ግን አንድ ነው።
እንግዲህ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የአካሉ ብልቶች ናችሁ።
እርሷም ሁሉን ነገር በሁሉም ረገድ የሚሞላው፣ የርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት።
በአንድ ሐሳብ፣ በአንድ ፍቅር፣ በአንድ መንፈስና በአንድ ዐላማ በመሆን ደስታዬን ፍጹም አድርጉልኝ።
እንግዲህ እኛ ብስለት ያለን ሁላችን ነገሮችን በዚህ ሁኔታ ማየት ይኖርብናል፤ በአንዳንድ ነገር የተለያየ አስተሳሰብ ቢኖራችሁ፣ እግዚአብሔር እርሱንም ይገልጥላችኋል።