Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘፀአት 29:40

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋራ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ምርጥ ዱቄትን ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋራ ለውስና ሩብ ሂን ወይንን ደግሞ የመጠጥ መሥዋዕት በማድረግ አቅርብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

34 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕቆብም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፤ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት።

በማግስቱም መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ፣ እነሆ፤ ከኤዶም በኩል ውሃ እየጐረፈ መጣ፤ ምድሪቱም ውሃ በውሃ ሆነች።

አንድ ጎሞር የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ነው።

አንዱን ጠቦት በማለዳ፣ ሌላውን በማታ አቅርብ።

ሌላውን የበግ ጠቦት በማለዳው እንደ ቀረበው ተመሳሳይ ከሆነው የእህልና የመጠጥ መሥዋዕት ጋራ በማታ ሠዋው፤ ይህም ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።

ዐምስት መቶ ሰቅል ብርጕድ ውሰድ፤ ሁሉም እንደ መቅደሱ ሰቅልና አንድ የሂን መስፈሪያ የወይራ ዘይት ይሁን፤

በሸለቆው በሚገኙት ለስላሳ ድንጋዮች ውስጥ ያሉት ጣዖቶች የአንቺ ናቸው፤ እነርሱም ዕጣ ፈንታዎችሽ ናቸው፤ ርግጥ ነው፣ በእነርሱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፤ የእህል ቍርባንም አቅርበሻል፤ ታዲያ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዝም እላለሁን?

ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር ባስገባኋቸው ጊዜ፣ ከፍ ያለውን ኰረብታ ሁሉና የለመለመውን ዛፍ ሁሉ ተመለከቱ፤ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ፤ ቍርባናቸውን በማቅረብ ቍጣዬን አነሣሡ፤ መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣናቸውን ዐጠኑ፤ የመጠጥ ቍርባናቸውንም አፈሰሱ።

የምትጠጣውንም ውሃ አንድ ስድስተኛ ሂን ለክተህ አስቀምጥ፤ በተወሰነ ጊዜ ትጠጣዋለህ።

በበዓላት፣ በወር መባቻና በሰንበታት፣ ለእስራኤል ቤት በተወሰኑት በዓላት ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ማቅረብ የገዢው ኀላፊነት ነው፤ ለእስራኤል ቤት ማስተስረያ እንዲሆንም የኀጢአት መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባል።’

ለአንዱ ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ለአንድ አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን አድርጎ፣ ለእያንዳንዱም ኢፍ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ዐብሮ ያቅርብ።

በበዓላትና በተወሰኑት በዓላት፣ ከወይፈኑ ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ከአውራ በጉም ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚያቀርበው የእህል ቍርባን ግን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።

ከዚህም ጋራ አንድ ስድስተኛ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት መለወሻም የሚሆን የሂን መስፈሪያ ሢሶ ዘይት አድርገህ በየማለዳው የእህል ቍርባን አቅርብ፤ ይህን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ማቅረብም የዘላለም ሥርዐት ነው።

ከአውራ በጉ ጋራ የሚቀርበው የእህል ቍርባን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚቀርበውም የእህል ቍርባን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።

ከወይፈኑ ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ከአውራው በግም ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚቀርበው የእህል ቍርባን ደግሞ ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።

የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈስሱም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሠኘውም፤ እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ። ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም።

ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።

የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን፣ ከእግዚአብሔር ቤት ተቋርጧል፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚያገለግሉ፣ ካህናት ያለቅሳሉ።

በምሕረቱ ተመልሶ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን እንዲተርፋችሁ፣ በረከቱን ይሰጣችሁ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

ከዚህም ጋራ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን ሁለት ዐሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ለእህል ቍርባን፣ አንድ አራተኛ የሂን መስፈሪያ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን አቅርቡ።

በመሠዊያው ላይ ያለው እሳት ዘወትር ይንደድ፤ ምን ጊዜም አይጥፋ።

ይህም የተፈጸመው ሆነ ተብሎ ሳይሆንና ማኅበረ ሰቡም ሳያውቀው ከሆነ፣ ማኅበረ ሰቡ በሙሉ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጎ አንድ ወይፈን በእሳት ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚሁም ጋራ ሥርዐቱ የሚጠይቀውን የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ደግሞም ለኀጢአት መሥዋዕት ተባዕት ፍየል ያቅርብ።

እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ አዘጋጁ፤ ይህንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያለው አድርጋችሁ አቅርቡ።

ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ በየሰንበቱ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

በዚህም ዐይነት ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሆኖ በየዕለቱ ለሰባት ቀን በእሳት ለሚቀርብ መሥዋዕት የምግብ ቍርባን አዘጋጁ፤ ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋራ ሆኖ በተጨማሪ ይቀርባል።

ከዚህም ጋራ ተወቅጦ በተጠለለ በሂን አንድ አራተኛ የወይራ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ።

ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

“የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት፣ ደስ የሚያሰኝ ሽታ ባለው ዕጣን፣ ዘወትር በሚቀርበው በእህል ቍርባንና በቅብዐ ዘይቱ ላይ ኀላፊነት ይኖረዋል፤ እንደዚሁም ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ መቅደሱንና ዕቃዎቹን ጭምር ይጠብቃል።”

የመሥዋዕታቸውን ሥብ የበሉ፣ የመጠጥ ቍርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው? እስኪ ይነሡና ይርዷችሁ! እስኪ መጠለያ ይስጧችሁ!

ነገር ግን በእምነታችሁ መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ እንደ መጠጥ ቍርባን ብፈስስ እንኳ ከሁላችሁ ጋራ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች