Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘፀአት 29:32

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሮንና ወንዶች ልጆቹ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ የአውራውን በግ ሥጋና በሌማት ያለውን ዳቦ ይብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእግዚአብሔር ፊት በሌማት ካለው ያለ እርሾ ከተጋገረው ቂጣ፣ ዳቦ፣ በዘይት የተሠራ ዕንጐቻና ኅብስት ውሰድ።

“የክህነቱን አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ቀቅለው።

ለክህነታቸውና ለመቀደሳቸው ማስተስረያ የሆኑትን እነዚህን መሥዋዕቶች ይብሉ፤ የተቀደሱ ስለ ሆኑ ሌላ ማንም አይብላቸው።

ሙሴም አሮንና ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉት፤ በዚያም፣ ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ተብዬ በታዘዝሁት መሠረት፣ በክህነት መስጫው መሥዋዕት መሶብ ውስጥ ካለው ቂጣ ጋራ ብሉት፤

ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፤ ለካህናት እንጂ ለርሱም ሆነ ዐብረውት ለነበሩት ያልተፈቀደውን ኅብስተ ገጽ በላ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች