የደረት ኪሱም ቀለበቶች፣ የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋራ እንዳይላቀቅ፣ ከመታጠቂያው ጋራ በማገናኘት በሰማያዊ ገመድ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋራ ይያያዙ።
በኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎች።
ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶች አበጅተህ ከኤፉዱ መታጠቂያ ከፍ ብሎ ከመጋጠሚያው አጠገብ ካለው በኤፉዱ ፊት ለፊት፣ በትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ግርጌ ጋራ አያይዘው።
“አሮን ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርድ መስጫው ደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም።
“የኤፉዱ ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ጨርቅ ይሁን፤
ከመጠምጠሚያው ጋራ እንዲያያዝ ሰማያዊ ፈትል እሰርበት፤ እርሱም በመጠምጠሚያው ፊት በኩል ይሁን።
በጥበብ የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር ከኤፉድ ጋራ አንድ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን።
በመቅደሱ ሲያገለግሉ የሚለበሱት የተፈተሉት ቀሚሶች፣ ለካህኑ ለአሮን የተቀደሱት ቀሚሶችና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚያደርጓቸው ቀሚሶች ናቸው።
“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ በየልብሳችሁ ጫፍ ላይ ዘርፍ አድርጉ፤ እያንዳንዱም ዘርፍ ሰማያዊ ጥለት ይኑረው።