ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ በኤፉዱ ትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ጋራ አያይዛቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቹን በትከሻው ላይ ይሸከማቸው።
በርግጥ ትከሻዬ ላይ በደረብሁት፣ እንደ አክሊልም ራሴ ላይ በደፋሁት ነበር።
በዚያ ጊዜ በራእይ ተናገርህ፤ ታማኝ ሕዝብህንም እንዲህ አልህ፤ “ኀያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁት፤ ከሕዝብ መካከል የተመረጠውንም ከፍ ከፍ አደረግሁት።
“ይህን ቀን መታሰቢያ ታደርጉታላችሁ፤ በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ሆኖ የእግዚአብሔር በዓል አድርጋችሁ አክብሩት።
የእግዚአብሔር ሕግ በከንፈራችሁ ላይ እንዲሆን ይህ በዓል ለእናንተ በእጃችሁ ላይ እንደ ታሰረ ምልክት፣ በእግራችሁ ላይ እንደሚገኝ መታሰቢያ ይሆንላችኋል። እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ ከግብጽ አውጥቷችኋልና።
የእጅ ጥበብ ባለሙያ ማኅተም እንደሚቀርጽ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ቅረጽ፤ ከዚያም ድንጋዮቹን በወርቅ ፈርጥ ክፈፋቸው፤
“አሮን ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርድ መስጫው ደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም።
መተሳሰር እንዲችል ሆኖ፣ ዳርና ዳር ከሚገኙት ከሁለቱ ጐኖች ጋራ የተያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት።
እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ድነቴም ሆኗል።”
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ፈጽሞ አይታክቱም። እናንተ ወደ እግዚአብሔር አቤት፣ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤
ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።
ከኅብስቱ ጋራ የመታሰቢያ ድርሻ ሆኖ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት እንዲሆን ንጹሕ ዕጣን በእያንዳንዱ ረድፍ ላይ አኑር።
ይህን ያደረገውም፣ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት ነው፤ ይህም ከአሮን ዘር በቀር ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ዕጣን እንዳያጥን አለዚያ ግን፣ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ እንደሚሆን ለእስራኤላውያን የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነበር።
ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ከሻለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤላውያን መታሰቢያ እንዲሆን ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡት።
ምሕረቱን በማስታወስ፣ ብላቴናውን እስራኤልን ረድቷል፤
ይህንም ያደረገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየት፣ ቅዱስ ኪዳኑን ለማስታወስ፣
ቆርኔሌዎስም በድንጋጤ ትኵር ብሎ እያየው፣ “ጌታ ሆይ፤ ምንድን ነው?” አለው። መልአኩም እንዲህ አለው፤ “ጸሎትህና ምጽዋትህ ለመታሰቢያነት ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐርጎልሃል።
ከባረከ በኋላ ቈርሶ፣ “ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ለመታሰቢያዬም አድርጉት” አለ።
ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በርሱ ተጠብቆ ያለ ሥጋት ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወድደውም ሰው በትከሻዎቹ መካከል ያርፋል።”
የዮርዳኖስ ወንዝ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መቆሙን፣ እንዲሁም ታቦቱ ዮርዳኖስን በሚሻገርበት ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መቆሙን፣ እነዚህ ድንጋዮች ለእስራኤል ሕዝብ የዘላለም መታሰቢያ መሆናቸውን ንገሯቸው።”