አደባባዩ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱ ዐምሳ ክንድ ሆኖ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ማግ ቁመታቸው ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎችና የንሓስም መቆሚያዎች ያሉት ይሁን።
“በቀጭኑ ከተፈተለ የበፍታ ድርና በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ፤ እጀ ብልኅ ሠራተኛም ኪሩቤልን ይጥለፍባቸው።
በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ ኵላቦችና የንሓስ መቆሚያዎች ይኑሯቸው።
ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከንሓስ የተሠሩ ይሁኑ።