ዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች እኩል ይሁኑ፤ የእያንዳንዱ ርዝመት ሠላሳ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ ይሁን።
የድንኳኑ መጋረጃዎች በሁለቱም ጐኖች አንድ ክንድ ርዝመት ይኖራቸዋል፤ የተረፈውም የማደሪያውን ድንኳን ጐኖች እንዲሸፍን ሆኖ ይንጠለጠላል፤
መጋረጃዎች ሁሉ እኵል ይሁኑ፤ የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ ወርዱም አራት ክንድ ይሁን።
“ማደሪያ ድንኳኑን ከላይ ሆነው የሚሸፍኑ በጠቅላላ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎች ሥራ።
ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ፣ እንደዚሁም ስድስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርገህ ስፋቸው፤ ከማደሪያው ድንኳን ፊት ለፊት ስድስተኛውን መጋረጃ ዕጠፍና በላዩ ላይ ደርበው።