በሌላው ጐን ላሉት ዐምስት፣ በማደሪያው ድንኳን ዳር በምዕራብ በኩል ባሉት ወጋግራዎች ዐምስት አብጅ።
“ደግሞም ከግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን አብጅ፤ በአንድ በኩል ላሉት የማደሪያው ድንኳን ወጋግራዎች ዐምስት፣
መካከለኛው አግዳሚ በወጋግራዎቹ መካከል ከጫፍ እስከ ጫፍ ይተላለፍ።
በዳር በኩል ይኸውም በስተምዕራብ ጫፍ ባለው ማደሪያው ድንኳን ስድስት ወጋግራዎችን ሠሩ።