ለማደሪያው ድንኳን ክፍል በደቡብ በኩል ሃያ ወጋግራዎችን ሥራ።
መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ? የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?
“ለማደሪያው ድንኳን ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን አብጅ።
ሁለት ጕጦችም ጐን ለጐን ይሁኑለት፤ የማደሪያውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚሁ መልክ አብጅ።
ከሥራቸው የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ፤ በእያንዳንዱ ጕጠት ሥር አንድ መቆሚያ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ።