በአንድ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ እንዲሁም በሌላ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ።
ከዚያም ዐምሳ የንሓስ ማያያዣዎችን ሥራ፤ ድንኳኑን አንድ ወጥ አድርጎ ለማያያዝ በቀለበቶቹ ውስጥ ጨምራቸው።
ከዳር በኩል ባለው መጋረጃ ጠርዝ ላይ፣ ከሰማያዊ ጨርቅ የተሠሩ ቀለበቶች አድርግ፤ በሌላውም የመጋረጃ ጠርዝ ላይ እንዲሁ አድርግ።
ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ፣ እንደዚሁም ስድስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርገህ ስፋቸው፤ ከማደሪያው ድንኳን ፊት ለፊት ስድስተኛውን መጋረጃ ዕጠፍና በላዩ ላይ ደርበው።
በአንደኛው መጋረጃ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን በሌላው ተጋጥሞ ከተሰፋው በስተመጨረሻ ካለው መጋረጃ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን እርስ በርሳቸው ትይዩ በማድረግ ሠሩት።