የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ተራራውን እስከ ስድስት ቀን ድረስ ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር በደመናው ውስጥ ሆኖ ሙሴን ጠራው።
ከደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው፤ እነርሱም ትእዛዙንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ።
አሮንም ለመላው የእስራኤል ማኅበር ሲናገር ሳለ ወደ ምድረ በዳው ተመለከቱ፤ በዚያም የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ላይ ተገልጦ ይታይ ነበር።
በሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ ምክንያቱም በዚያ ቀን በሕዝቡ ፊት እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳል።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ጋራ ስናገር ሕዝቡ እንዲሰሙኝና እምነታቸውን ምን ጊዜም በአንተ ላይ እንዲጥሉ በከባድ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ” ከዚያም ሙሴ ሕዝቡ ያሉትን ለእግዚአብሔር ነገረው።
ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በዚያ ቀን አንተም ሆንህ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህ ሆነ ሴት አገልጋይህ፣ ወይም እንስሳትህ፣ ወይም በደጅህ ያለ መጻተኛ ምንም ሥራ አትሠሩም።
ለእስራኤላውያን የእግዚአብሔር ክብር በተራራው ጫፍ ላይ እንደሚባላ እሳት ሆኖ ይታይ ነበር።
ከዚያም እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፣ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤
በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንደሚታየው ቀስተ ደመና በዙሪያው ያለው ጸዳል እንዲሁ ነበር። ይህም የእግዚአብሔር ክብር መልክ አምሳያ ነበረ። ባየሁትም ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፤ የአንድ ተናጋሪን ድምፅ ሰማሁ።
ከዚህ በኋላ፣ ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፤ ከዚያ ሲወጡም ሕዝቡን ባረኩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ።
ሙሴም፣ “የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥላችሁ ዘንድ፣ እንድታደርጉት እግዚአብሔር ያዘዛችሁ ይህ ነው” አለ።
መላው ማኅበር ግን በድንጋይ ሊወግሯቸው ተነጋገሩ፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ክብር በመገናኛው ድንኳን ለእስራኤላውያን ሁሉ ተገለጠ።
ማኅበሩም ሙሴንና አሮንን ለመቃወም በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን ዘወር ሲሉ ደመና ድንኳኑን በድንገት ሸፍኖት አዩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠ።
በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ይሰጠን ዘንድ፣ “በጨለማ ብርሃን ይብራ” ያለው እግዚአብሔር ብርሃኑን በልባችን አብርቷልና።
በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከበስተ ኋላዬ ሰማሁ፤