ነገር ግን የከፋ ጕዳት ቢደርስ ሕይወት በሕይወት፣
ማንኛውም ሰው በባልንጀራው ላይ ጕዳት ቢያደርስ፣ የዚያው ዐይነት ጕዳት ይፈጸምበት፤
ይኸውም ስብራት በስብራት፣ ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ ማለት ነው። በሌላው ሰው ላይ ያደረሰው ጕዳት በርሱም ላይ ይድረስበት፤
“ ‘ነፍስ ያጠፋን፣ በመግደል ወንጀል ተጠያቂ የሆነን ሰው ጉማ አትቀበሉ፤ ፈጽሞ መሞት አለበት።
ርኅራኄ አታድርግ፤ ሕይወት በሕይወት፣ ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር ይመለስ።