በአፍንጫህ እስትንፋስ፣ ውሆች ተቈለሉ፤ ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ።
ከእግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫው ከሚወጣው፣ ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣ የባሕር ወለል ታየ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።
በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤ በቍጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ።
የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል።
ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።
እስራኤላውያን ግን ውሃው ግራና ቀኝ እንደ ግድግዳ ሆኖ፣ በደረቅ ምድር ባሕሩን ተሻገሩ።
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
እነሆ፤ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬም ሰምቶ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ በገዛ አገሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።’ ”
ተራሮች አዩህ፤ ተጨነቁም፤ የውሃ ሞገድ ዐልፎ ሄደ፤ ቀላዩ ደነፋ፤ ማዕበሉንም ወደ ላይ አነሣ።
ታላላቅ ውሆችን በመናጥ፣ ባሕሩን በፈረሶችህ ረገጥህ።
ከዚያም በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያስወግደውና በምጽአቱም ክብር ፈጽሞ የሚያጠፋው ዐመፀኛ ይገለጣል።
የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ገና እግራቸውን በዮርዳኖስ ውሃ ውስጥ እንዳስገቡ፣ ቍልቍል የሚወርደው ውሃ ወዲያውኑ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።”
ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ “አዳም” ተብላ እስከምትጠራው ሩቅ ከተማ ድረስ በመከማቸት እንደ ክምር ተቈለለ፤ ቍልቍል ወደ ዓረባ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውሃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ተሻገሩ።