እስራኤላውያን ውሃው በግራና በቀኝ እንደ ግድግዳ ሆኖ በየብስ በባሕሩ ውስጥ ዐለፉ።
ከኤልያስ፣ የወደቀውንም ካባ ይዞ ውሃውን መታና፣ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” አለ። ውሃውን ሲመታውም ውሃው በግራና በቀኝ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።
ኤልያስም ካባውን አውልቆ ጠቀለለውና ውሃውን መታበት፤ ከዚያም ውሃው ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ሁለቱም በደረቅ ምድር ተሻገሩ።
በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልህ፤ ያሳደዷቸውን ግን በኀይለኛ ውሃ ውስጥ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ውስጥ ወረወርሃቸው።
ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው።
ቀይ ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
ባሕሩን የብስ አደረገው፤ ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ ኑ፣ በርሱ ደስ ይበለን።
ምንጮችንና ፈሳሾችን ያፈለቅህ አንተ ነህ፤ ሳያቋርጡ የሚፈስሱትንም ወንዞች አደረቅህ።
ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።
እስራኤላውያን ግን ውሃው ግራና ቀኝ እንደ ግድግዳ ሆኖ፣ በደረቅ ምድር ባሕሩን ተሻገሩ።
የፈርዖን ፈረሶች፣ ሠረገሎቹና ፈረሰኞቹ ወደ ባሕሩ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሃ በላያቸው ላይ መለሰባቸው፤ እስራኤላውያን ግን በባሕሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ተሻገሩ።
በአፍንጫህ እስትንፋስ፣ ውሆች ተቈለሉ፤ ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ።
እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።
እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ እንደ ሆነው ሁሉ፣ ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣ እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።
በባሕር ውስጥ መንገድ፣ በማዕበል ውስጥ መተላለፊያ ያበጀ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
የዳኑት እንዲሻገሩ ባሕሩን፣ የታላቁን ጥልቅ ውሆች ያደረቅህ፣ በጥልቁም ውስጥ መንገድ ያበጀህ፣ አንተ አይደለህምን?
የከበረው ኀያል ክንድ፣ በሙሴ ቀኝ እጅ ላይ እንዲያርፍ አደረገ፤ ለራሱ የዘላለም ዝና እንዲሆንለት፣ ውሆችን በፊታቸው ከፈለ።
ፈረስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ ሁሉ፣ እነርሱንም በጥልቁ ውስጥ አሳልፎ መራቸው፤ ስለዚህም አልተሰናከሉም፤
እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፣ ‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’
ከፊሃሒሮት ተነሥተው በባሕሩ ውስጥ በማለፍ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ ከዚያም በኤታም ምድረ በዳ ሦስት ቀን ተጕዘው በማራ ሰፈሩ።
ወንድሞች ሆይ፤ አባቶቻችን ሁሉ ከደመናው በታች እንደ ነበሩና በባሕሩ ውስጥ እንደ ተሻገሩ ታውቁ ዘንድ እፈልጋለሁ።
ሕዝቡ በደረቅ መሬት እንደሚኬድ ቀይ ባሕርን በእምነት ተሻገሩ፤ ግብጻውያን ግን እንደዚሁ ለማድረግ ሲሞክሩ ሰጠሙ።
ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ “አዳም” ተብላ እስከምትጠራው ሩቅ ከተማ ድረስ በመከማቸት እንደ ክምር ተቈለለ፤ ቍልቍል ወደ ዓረባ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውሃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ተሻገሩ።
የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናትም፣ ሕዝቡ ሁሉ፣ ማለት እስራኤል በሙሉ ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል በደረቁ ምድር ላይ ቀጥ ብለው ቆመው ነበር።
‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስ በደረቅ ምድር ተሻገረ’ ብላችሁ ንገሯቸው፤
በጎቻችንን እየጠበቅን ዐብረናቸው ባሳለፍነው ጊዜ ሁሉ፣ ቀንም ሆነ ሌሊት በዙሪያችን ዐጥር ሆነውን ነበር።