Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘፀአት 10:6

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የአንተን፣ የሹማምትህንና የግብጻውያንን ቤቶች ሁሉ ይሞሏቸዋል፤ ይህም አባቶችህም ሆኑ ቅድመ አያቶችህ በዚህች ምድር ከሰፈሩበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከቶ አይተውት የማያውቁት ነው።’ ” ሙሴም ተመለሰና ከፈርዖን ተለይቶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አይሆንም፤ ወንዶቹ ብቻ እንዲሄዱና እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አድርጉ፤ የጠየቃችሁት ይህንኑ ነው።” ከዚያም ሙሴና አሮን ከፈርዖን ፊት እንዲወጡ ተደረገ።

በግብጽ ምድር ሁሉ ከዚህ በፊት ያልተሰማ ወደ ፊትም የማይሰማ ታላቅ ዋይታ ይሆናል።

ሹማምትህ በሙሉ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ እጅ እየነሡም ‘አንተም ሆንህ የምትመራቸው ሰዎች በሙሉ ውጡልን’ ብለው ይለምኑኛል፤ እኔም ከዚያ በኋላ እሄዳለሁ።” ከዚያም ሙሴ በታላቅ ቍጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።

ሕዝቤ እንዲሄዱ ባትለቅቃቸው፣ በአንተና በሹማምትህ ላይ፣ በሕዝብህና በቤቶችህ ላይ የዝንብ መንጋ እሰድዳለሁ። ያረፉበት መሬት እንኳ ሳይቀር፣ የግብጻውያን ቤቶች ሁሉ ዝንብ ብቻ ይሆናሉ።

አባይ በጓጕንቸሮች ይሞላል፤ ወጥተውም ወደ ቤተ መንግሥትህና ወደ መኝታ ክፍልህ፣ ወደ ዐልጋህም ወደ ሹማምቶችህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሖቃዎችህ ይገባሉ።

ስለዚህ ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብጽ ላይ ወርዶ የማያውቅ አስከፊ የበረዶ ማዕበል እልካለሁ።

በረዶ ወረደ፤ መብረቅም አብረቀረቀ፤ ግብጽ አገር ከሆነችበት ዘመን አንሥቶ በምድሪቱ ሁሉ እንደዚህ ያለ አስከፊ ማዕበል ሆኖ አያውቅም።

ይህም የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። የንጋት ብርሃን በተራሮች ላይ እንደሚወጣ፣ ኀያልና ብዙ ሰራዊት ይመጣል፤ ከጥንት እንዲህ ዐይነት ከቶ አልነበረም፤ በሚመጡትም ዘመናት እንዲህ ዐይነት ከቶ አይሆንም።

ከተማዪቱን ይወርራሉ፤ በቅጥሩም ላይ ይዘልላሉ፤ በቤቶች ላይ ዘልለው ይወጣሉ፤ እንደ ሌባም በመስኮት ይገባሉ።

የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ ግብጽን ለቅቆ በእምነት ወጣ፤ የማይታየውንም እንዳየው አድርጎ በመቍጠር በሐሳቡ ጸና።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች