በግብጽም፣ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ አዲስ ንጉሥ ነገሠ።
ሕዝቡን እንዲጠሉ፣ በባሪያዎቹም ላይ እንዲያሤሩ ልባቸውን ለወጠ።
“ሂድና የእስራኤልን አለቆች ሰብስበህ፣ ‘የአባቶቻችሁ የአብርሃም፣ የይሥሐቅና የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፤ ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብጽ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ።
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ “በግብጽ አገር የሚኖሩትን የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ፤ ከአሠሪዎቻቸው ጭካኔ የተነሣ የሚያሰሙትንም ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ሥቃያቸውንም ተረድቻለሁ።
አሁንም የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደርሷል፤ ግብጻውያን የሚያደርሱባቸውን ግፍ አይቻለሁ።
በዚያችም ከተማ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ይኖር ነበር፤ በጥበቡም ከተማዋን አዳናት፤ ነገር ግን ያን ድኻ ማንም አላስታወሰውም።
ከዚያ በኋላ ‘ስለ ዮሴፍ የማያውቅ አዲስ ንጉሥ በግብጽ ነገሠ።’
እርሱም ሕዝባችንን በተንኰሉ አስጨነቀ፤ ገና የተወለዱ ሕፃናታቸውም ይሞቱ ዘንድ ወደ ውጭ አውጥተው እንዲጥሏቸው አስገደዳቸው።
ግብጻውያን ግን ከባድ ሥራ በማሠራት አንገላቱን፤ አሠቃዩንም።
ያ ሁሉ ትውልድ ወደ አባቶቹ ከተከማቸ በኋላ እግዚአብሔርንም ሆነ እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሣ።