Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



አስቴር 8:7

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሥ ጠረክሲስም ለንግሥት አስቴርና ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እነሆ ሐማ አይሁድን ለማጥፋት ስላቀደ፣ ቤት ንብረቱን ለአስቴር ሰጥቻለሁ፤ እርሱንም በዕንጨት ላይ ሰቅለውታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጠረክሲስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የጽሑፍ ክስ መሠረቱባቸው።

ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሐማን ሰቀሉት፤ ከዚያም የንጉሡ ቍጣ በረደ።

ከዚያም ንጉሡን በቅርብ ከሚያገለግሉት ጃንደረቦች አንዱ የሆነው ሐርቦና፣ “እነሆ ቁመቱ ዐምሳ ክንድ የሆነ ግንድ በሐማ ቤት አጠገብ ተተክሏል፤ ይህን ያዘጋጀው ንጉሡን ለማዳን በጎ ነገር ለተናገረው ለመርዶክዮስ ነው” አለ። ንጉሡም፣ “በዚሁ ላይ ስቀሉት” አለ።

በዚያ ዕለት ንጉሥ ጠረክሲስ የአይሁድን ጠላት የሐማን ቤት ንብረት ለንግሥት አስቴር ሰጣት፤ አስቴርም መርዶክዮስ እንዴት እንደሚዛመዳት ለንጉሡ ነግራው ስለ ነበር፣ መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ ዘንድ ቀረበ።

ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤ የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል።

“በዕንጨት ላይ የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ፣ ክርስቶስ ስለ እኛ ርግማን ሆኖ ከሕግ ርግማን ዋጅቶናል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች