Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



አስቴር 8:11

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የንጉሡም ዐዋጅ በየከተማው የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ እንዲሰበሰቡና ራሳቸውን ከጥቃት እንዲከላከሉ እንዲሁም በራሳቸው፣ በሚስቶቻቸውና በልጆቻቸው ላይ አደጋ የሚያደርስባቸውን የየትኛውንም ዜጋ ወይም አውራጃ የታጠቀ ኀይል እንዲያጠፉ፣ እንዲገድሉ፣ እንዲደመስሱና የጠላቶቻቸውን ሀብት እንዲዘርፉ ፈቀደላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር፣ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ሴትና ሕፃን ሳይባል አይሁድ ሁሉ በዚያ ዕለት እንዲጠፉ፣ እንዲገደሉና እንዲደመሰሱ፣ ሀብታቸውም እንዲዘረፍ ደብዳቤ ለንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ በመልእክተኞች እጅ ተላከ።

በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ ግን በዐሥራ ሦስተኛውና በዐሥራ አራተኛው ቀን ተሰብስበው ነበር፤ ከዚያም በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ዐረፉ፤ ዕለቱንም የተድላና የደስታ ቀን አድርገው ዋሉ።

አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤ በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሽው ድርጊት፣ የእጅሽን የሚሰጥሽ ብፁዕ ነው፤

ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት ሐሤት ያድርጉ፤ ደስታንና ፍሥሓን የተሞሉ ይሁኑ።

ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣ በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰድደዋለሁ።

ከሜዳ ላይ ዕንጨት መልቀም፣ ከዱርም ዛፍ መቍረጥ አያስፈልጋቸውም፤ የጦር መሣሪያቸውን በመማገድ ይጠቀማሉና። የዘረፏቸውን ይዘርፋሉ፤ የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች