በንጉሡ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁና የምፈልገውን ሊሰጠኝና ልመናዬንም ሊፈጽምልኝ ንጉሡን ደስ ካሠኘው፣ ንጉሡና ሐማ በማዘጋጅላቸው ግብዣ ላይ ነገ ይገኙልኝ። ከዚያም እኔ ለንጉሡ ጥያቄ መልስ እሰጣለሁ።”
ንግሥት አስጢንም በንጉሥ ጠረክሲስ ቤተ መንግሥት እንደዚሁ ለሴቶች ግብዣ አድርጋ ነበር።
ሐማም፣ “ምን ይህ ብቻ” አለ፤ “ንግሥት አስቴር ባዘጋጀችው ግብዣ ላይ ከንጉሡ ጋራ እንድገኝ የጋበዘችው ሰው አንድ እኔ ብቻ ነኝ፤ ነገም ከንጉሡ ጋራ ጋብዛኛለች።
አስቴርም እንዲህ ስትል መለሰች፤ “ልመናዬም፣ ጥያቄዬም ይህ ነው፤
ስለዚህ ንጉሡና ሐማ ከንግሥት አስቴር ጋራ ለመጋበዝ ሄዱ፤
ከዚያም ንግሥት አስቴር እንዲህ ስትል መለሰች፤ “ንጉሥ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼና ግርማዊነትህን ደስ የሚያሰኝ ከሆነ፣ ሕይወቴን ታደጋት፤ ልመናዬ ይህ ነው፤ ሕዝቤን አትርፍ፤ ጥያቄዬም ይኸው ነው።
እንዲህም አለች፤ “ንጉሡን ደስ የሚያሠኘውና እኔም በፊቱ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ጕዳዩም በንጉሡ ዘንድ ተገቢ ሆኖ ከተገኘና በእኔም ደስ ከተሠኘ፣ የአጋጋዊው የሐመዳቱ ልጅ ሐማ በንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ የሚገኙትን አይሁድ ለማጥፋት የሸረበውን ሤራና የጻፈውን ደብዳቤ የሚሽር ትእዛዝ ይጻፍ።
ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ እግዚአብሔር ግን ርምጃውን ይወስንለታል።