Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



አስቴር 3:5

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሐማም መርዶክዮስ ወድቆ እንዳልሰገደለትና እንዳላከበረው ሲያይ እጅግ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አገልጋዮቹ የንጉሡን ትእዛዝ በነገሯት ጊዜ ግን፣ ንግሥት አስጢን መሄድ አልፈለገችም። ከዚያም ንጉሡ በጣም ተቈጣ፤ እጅግም ተናደደ።

ንጉሡ ስለ እርሱ ይህ እንዲደረግለት አዝዞ ስለ ነበር፣ በንጉሡ በር ያሉት የመንግሥቱ ሹማምት ሁሉ ለሐማ ተንበርክከው እጅ በመንሣት አክብሮታቸውን ይገልጡለት ነበር። መርዶክዮስ ግን ወድቆ አልሰገደለትም፤ አክብሮትም አላሳየውም።

ይህንም በየቀኑ ይነግሩት ነበር፤ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም። አይሁዳዊ መሆኑን ነግሯቸው ስለ ነበር፣ የመርዶክዮስ ባሕርይ እስከ መቼ ሊቀጥል እንደሚችል ለማየት ሲሉ ይህንኑ ለሐማ ነገሩት።

ሐማ በዚያ ቀን ደስ ብሎትና መንፈሱ ረክቶ ወጣ፤ ነገር ግን መርዶክዮስን በንጉሡ በር ላይ ሲያየው ከተቀመጠበት አለመነሣቱንና በፊቱም አለመንቀጥቀጡን ሲመለከት፣ ቍጣው በመርዶክዮስ ላይ ነደደ።

ቂሉን ሰው ብስጭት ይገድለዋል፤ ቂሉንም ቅናት ያጠፋዋል።

ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል።

ቂል ሰው ቍጣው ወዲያውኑ ይታወቅበታል፤ አስተዋይ ሰው ግን ስድብን ንቆ ይተዋል።

ግልፍተኛ ሰው ቅጣትን መቀበል ይገባዋል፤ በምሕረት ካለፍኸው ሌላም ጊዜ አይቀርልህም።

ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው “ፌዘኛ” ይባላል፤ በጠባዩም እብሪተኛ ነው።

ሞኞች በብዙ የክብር ስፍራዎች ሲቀመጡ፣ ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ስፍራ ሆነዋል።

ከዚያም ናቡከደነፆር በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ እጅግ ተቈጣ፣ ፊቱም ተለወጠባቸው፤ የእቶኑ እሳትም ቀደም ሲል ከነበረው ሰባት ዕጥፍ ተደርጎ እንዲነድድ አዘዘ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች