በዚህ ጊዜ ንጉሡ ከሌሎቹ ሴቶች ሁሉ ይበልጥ አስቴርን ወደዳት፤ ከሌሎቹ ደናግልም ሁሉ ይልቅ በርሱ ዘንድ ሞገስንና መወደድን አገኘች። ስለዚህ የእቴጌነት ዘውድ በራሷ ላይ ጫነላት፤ በአስጢንም ፈንታ ንግሥት አደረጋት።
ይኸውም ንግሥት አስጢን የደስ ደስ ያላት ነበረችና ውበቷ ለሕዝቡና ለመኳንንቱ እንዲታይ ዘውዷን ጭና ንጉሡ ፊት እንዲያመጧት ነበር።
በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ቴቤት በተባለው በዐሥረኛው ወር አስቴር ወደ ንጉሥ ጠረክሲስ ቤተ መንግሥት ተወሰደች።
በዚህ ጊዜ አንቺ ዝም ብትዪ፣ ለአይሁድ ርዳታና ትድግና ከሌላ ስፍራ ይመጣላቸዋል፤ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ አንቺ ንግሥት ለመሆን የበቃሽው ለዚህ ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”
ንጉሡ የሚጐናጸፈው ልብሰ መንግሥት፣ ንጉሡም የሚቀመጥበትና የንጉሡን ዘውድ በራሱ ላይ ያደረገ ፈረስ ይምጣለት።
የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሠኘው ይመራዋል።
የዱር ዛፎች ሁሉ ረዥሙን ዛፍ፣ ዝቅ ዝቅ ያለውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ የለመለመውን ዛፍ አደርቃለሁ፤ ደረቁንም አለመልማለሁ። “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔው አደርገዋለሁ።’ ”
እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከመኳንንቱ ጋራ ያስቀምጣቸዋል፤ የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል። “የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፣ ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጓል።