ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣ በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።
እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።
ሁለቱም የሚያመጡት መዓት፤ ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል?
ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤ ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል።
ስለዚህ በቅጽበት መዓት ይወርድበታል፤ በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።
የሰው ዕድል ፈንታ እንደ እንስሳት ነው፤ ሁለቱም ዕጣ ፈንታቸው አንድ ነው፤ አንዱ እንደሚሞት፣ ሌላውም እንዲሁ ይሞታል። ሁሉ አንድ ዐይነት እስትንፋስ አላቸው፤ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነው።
በወንጀል ላይ ባፋጣኝ ፍርድ ካልተሰጠ፣ የሰዎች ልብ ክፉን በማድረግ ዕቅድ ይሞላል።
ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም፤ በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤ በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣ ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም።
እንዲሁም እጅግ ያስገረመኝን ይህን የጥበብ ምሳሌ ከፀሓይ በታች አየሁ፤
ከሽብር ድምፅ የሚሸሽ፣ ወደ ጕድጓድ ይገባል፤ ከጕድጓድ የወጣም፣ በወጥመድ ይያዛል። የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፤ የምድርም መሠረት ተናወጠ።
ስለዚህ ይህ ኀጢአት፣ ተሰነጣጥቆ ሊወድቅ እንደ ደረሰ፣ ሳይታሰብ ድንገት እንደሚወድቅ ረዥም ቅጥር ይሆንባችኋል።
“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ብዙ ሕዝብ ይዤ፣ መረቤን በላይህ ላይ እጥላለሁ፤ በመረቤም ጐትተው ያወጡሃል።
ሲበርሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼ አወርዳቸዋለሁ። ስለ ክፉ ሥራቸውም፣ በጉባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ።
ነቢዩ ከአምላኬ ጋራ ሆኖ፣ የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ ዳሩ ግን በመንገዱ ሁሉ ወጥመድ፣ በአምላኩም ቤት ጠላትነት ይጠብቀዋል።
“እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊወስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።
ይህን ግን ዕወቁ፤ ሌባ በምን ሰዓት እንደሚመጣ ባለቤቱ ቢያውቅ ኖሮ፣ ቤቱ ሲቈፈር ዝም ብሎ ባላየ ነበር።
እርሱ፣ “በተወደደ ጊዜ ሰማሁህ፤ በድነት ቀን ረዳሁህ” ይላልና። እነሆ፤ የተወደደው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው።
ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።
ይኸውም ወደ አእምሯቸው ይመለሳሉ፤ ፈቃዱን ሊያስፈጽማቸው ምርኮኛ አድርጎ ከያዛቸው ከዲያብሎስ ወጥመድም ያመልጣሉ በማለት ነው።
ምንም እንኳ ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል በመልካም ሕይወት ኑሩ።
እነዚህ ሰዎች ግን ምንም በማያውቁት ነገር እየገቡ ይሳደባሉ፤ እነርሱም ለመያዝና ለመገደል እንደ ተወለዱ፣ በደመ ነፍስ እንደሚመሩና አእምሮ እንደሌላቸው እንስሳት የሚጠፉ ናቸው።