እርሱን የሚታዘዝ ሁሉ አይጐዳም፤ ጥበበኛም ልብ ትክክለኛውን ጊዜና ተገቢውን አሠራር ያውቃል።
ዘመኑን የተረዱና እስራኤላውያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤ በእነርሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው።
ወደ ትእዛዞችህ ስመለከት፣ በዚያ ጊዜ አላፍርም።
አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ የግብጽ ንጉሥ ያዘዛቸውን አልፈጸሙም፤ ወንዶቹንም ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው።
ጻድቃን ጕዳት አያገኛቸውም፤ ክፉዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው።
አስተዋይ ሰው ጥበብን ከፊቱ አይለያትም፤ የሞኝ ዐይኖች ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታሉ።
የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ፣ የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራ ያዘነብላል።
እነሆ፤ ሁሉ ነገር ከተሰማ ዘንድ፣ የነገሩ ሁሉ ድምዳሜ ይህ ነው፤ አምላክን ፍራ፤ ትእዛዞቹንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው ሁለንተናዊ ተግባሩ ነውና።
የጠቢብ ሰው ዐይኖች ያሉት በራሱ ውስጥ ነው፤ ሞኝ ግን በጨለማ ውስጥ ይራመዳል፤ ሆኖም የሁለቱም ዕድል ፈንታ፣ አንድ መሆኑን ተገነዘብሁ።
በአምላክ ፊት መሐላ ስለ ፈጸምህ፣ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር እልሃለሁ።
ጣዖትን መከተል በመውደዱ፣ ኤፍሬም ተጨቍኗል፤ በፍርድም ተረግጧል።
እርሱም፣ “እንግዲያውስ የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው።
ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው እንዲህ አሏቸው፤ “ከእግዚአብሔር ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ይገባ እንደ ሆነ እስኪ እናንተው ፍረዱ!
ጴጥሮስና ሌሎች ሐዋርያትም መልሰው እንዲህ አሉ፤ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል!
ከዚህ የተነሣ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር የፈቃዱን ዕውቀት በመንፈሳዊ ጥበብና መረዳት ሁሉ ይሞላችሁ ዘንድ ስለ እናንተ መጸለይና መለመን አላቋረጥንም፤
ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ ለበሰሉ ሰዎች ነው።