ብዙ ጊዜ አንተ ራስህ፣ ሌሎችን እንደ ረገምህ ልብህ ያውቃልና።
ንጉሡም መልሶ ሳሚን እንዲህ አለው፤ “በአባቴ በዳዊት ላይ ያደረግህበትን ክፉ ነገር ሁሉ ልብህ ያውቀዋል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ክፉ ሥራህ ብድሩን ይከፍልሃል።
የሚነገረውን ቃል ሁሉ ለማድመጥ አትሞክር፤ አለዚያ አገልጋይህ ሲረግምህ ትሰማ ይሆናል፤
እኔም ይህን ሁሉ በጥበብ ፈትኜ፣ “ጠቢብ ለመሆን ቈርጫለሁ” አልሁ፤ ይህ ግን ከእኔ የራቀ ነበር።
ክፉ ሐሳብ፣ ነፍስ መግደል፣ ማመንዘር፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ በሐሰት መመስከርና ስም ማጕደፍ ከልብ ይመነጫሉና።
በምላሳችን ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በርሷም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን።