ለአምላክ ስእለትን በተሳልህ ጊዜ ለመፈጸም አትዘግይ፤ በሞኞች ደስ አይለውምና፤ ስእለትህን ፈጽም።
ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን በምሄድበትም መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላው ምግብ፣ የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ
እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው።
ተነሥተን ወደ ቤቴል እንውጣ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፣ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።”
በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።
የጽድቅ ሕግህን ለመጠበቅ፤ ምያለሁ፤ ይህንኑ አጸናለሁ።
በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤ እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ።
“ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አቅርብ፤ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ።
ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተሳሉ፤ ስእለቱንም አግቡ፤ በርሱ ዙሪያ ያሉ ሁሉ፣ አስፈሪ ለሆነው ለርሱ እጅ መንሻ ያምጡ።
በችኰላ ስእለት መሳል፣ ከተሳሉም በኋላ ማቅማማት ለሰው ወጥመድ ነው።
እግዚአብሔር ራሱን ለግብጻውያን ይገልጣል፤ እነርሱም በዚያ ቀን እግዚአብሔርን ያውቁታል፤ በመሥዋዕትና በእህል ቍርባንም ያመልኩታል። ለእግዚአብሔር ስእለት ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽሙታል።
እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ ‘ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።’ ”
“በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳት እንዳታነድዱ፣ ምነው ከእናንተ አንዱ የቤተ መቅደሱን ደጅ በዘጋ ኖሮ! እኔ በእናንተ ደስ አይለኝም፤ ከእጃችሁም ምንም ዐይነት ቍርባን አልቀበልም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት በሚሳልበት ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሱን ግዴታ ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ ቃሉን ሳያጥፍ ያለውን ሁሉ መፈጸም አለበት።
“ለቀደሙት ሰዎች፣ ‘በሐሰት አትማል፤ በጌታ ፊት የማልኸውንም ጠብቅ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
በሚቃጠል መሥዋዕትና ለኀጢአት በሚቀርብ መሥዋዕት ደስ አልተሠኘህም።
ባያትም ጊዜ ልብሱን በመቅደድ፣ “ወይኔ ልጄ ጕድ አደረግሽኝ! ጭንቅም ላይ ጣልሽኝ፤ ማስቀረት የማልችለውን ስእለት ለእግዚአብሔር ተስያለሁና” ብሎ በሐዘን ጮኸ።