ይህ ደግሞ እጅግ ክፉ ነገር ነው፤ ሰው እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳል፤ የሚደክመው ለነፋስ ስለ ሆነ፣ ትርፉ ምንድን ነው?
ቤተ ሰቡን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፤ ቂልም ሰው የጠቢብ ባሪያ ይሆናል።
ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?
ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሁሉ፣ ለማግኘትም የደከምሁትን ድካም ሁሉ ሳስብ፣ ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነበር፤ ከፀሓይ በታች ምንም ትርፍ አልነበረም።
ሠራተኛ ከጥረቱ የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው?
ከፀሓይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፦ ይህም ለባለቤቱ ጕዳት የተከማቸ ሀብት፣
አረገዝን በምጥም ተጨነቅን፤ ነገር ግን ነፋስን ወለድን፤ ለምድርም ድነትን አላመጣንም፤ የዓለምን ሕዝብ አልወለድንም።
‘እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው ካህናቱ አልጠየቁም፤ ከሕጉ ጋራ የሚውሉት አላወቁኝም፤ መሪዎቹ ዐመፁብኝ፤ ነቢያቱም በበኣል ስም ተነበዩ፤ ከንቱ ነገሮችን ተከተሉ።
“ነፋስን ይዘራሉ፤ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ አገዳው ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም፤ እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ ባዕዳን ይበሉታል።
ሰው ዓለሙ ሁሉ የርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል?
ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ፤ ለዚህም እግዚአብሔር አብ ማረጋገጫ ማኅተሙን በርሱ ላይ ዐትሟልና።”
እንደ እነርሱ ላሉትና ከእነርሱም ጋራ በአገልግሎት ለሚደክሙ ሁሉ ታዘዙ።
ሊጠቅሟችሁ ወይም ሊያድኗችሁ የማይችሉ ምናምንቴ ነገሮችን አትከተሉ፤ ከንቱ ናቸውና።