ሰዎች ይደክሙበት ዘንድ አምላክ የሰጣቸውን ከባድ የሥራ ጫና አየሁ።
ከምድር ስለ ተገኘህ፣ ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ እንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤ ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”
የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የአምላክን ሥራ ማስተዋል አትችልም።
አምላክ፣ ደስ ለሚያሠኘው ሰው ጥበብን፣ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። ለኀጢአተኛ ግን፣ አምላክን ደስ ለሚያሠኘው ይተውለት ዘንድ፣ ሀብትን የመሰብሰብና የማከናወን ተግባር ይሰጠዋል። ይህም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
ወንድሞች ሆይ፤ ጥረታችንንና ድካማችንን ታስታውሳላችሁ፤ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እየሠራን የእግዚአብሔርን ወንጌል ሰበክንላችሁ።
ደግሞም የማንንም እንጀራ በነጻ አልበላንም፤ ነገር ግን ከእናንተ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እንደክምና እንሠራ ነበር፤