ሞኝ በጐዳና ሲሄድ ልበ ቢስ ነው፤ ጅል መሆኑንም ለማንም ይገልጻል።
አስተዋይ ሰው ሥራውን በዕውቀት ያከናውናል፤ ሞኝ ግን ቂልነቱን ይገልጣል።
ሞኝ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤ የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል።
የሞኝ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤ አፉም በትር ይጋብዛል።
በሥራ ብዛት ሕልም እንደሚታይ፣ ብዙ ቃል ባለበትም የሞኝ ንግግር ይገለጣል።
ይህን በመሰለ ብኩን ሕይወት ከእነርሱ ጋራ ስለማትሮጡ እንግዳ ሆኖባቸው በመደነቅ ይሰድቧችኋል።