Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



መክብብ 1:10

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ማንም፣ “እነሆ፤ ይህ አዲስ ነገር ነው!” ሊል የሚችለው አንዳች ነገር አለን? ቀድሞውኑ በዚሁ የነበረ ነው፤ ከእኛ በፊት የሆነ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቀድሞ ነገሮች መታሰቢያ የላቸውም፤ ወደ ፊት የሚመጡትም ቢሆኑ፣ ከእነርሱ በኋላ በሚተኩት አይታወሱም።

የነበረው ነገር እንደ ገና ይሆናል፤ የተደረገውም ተመልሶ ይደረጋል፤ ከፀሓይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።

ከዚያም ጥበብን፣ እብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ሐሳቤን መለስሁ፤ አስቀድሞ ከተደረገው በቀር፣ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል?

አሁን ያለው ሁሉ አስቀድሞ ስም የተሰጠው ነው፤ ሰው የሚሆነውም አስቀድሞ የታወቀ ነው፤ ከራሱ ይልቅ ከሚበረታ ጋራ፣ ማንም አይታገልም።

በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ አሳድደዋቸዋልና።

“እናንተ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ! ዐንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ።

ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደ ተቃወሙት፣ እነዚህ አእምሯቸው የጠፋባቸውና ከእምነት የተጣሉ ሰዎች ደግሞ እውነትን ይቃወማሉ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች