ይህን ስትነግሩኝ እግዚአብሔር ሰማ፤ እግዚአብሔርም አለኝ፤ “ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ያሉትም ሁሉ መልካም ነው።
“የሰለጰዓድ ልጆች ጥያቄ ትክክል ነው፤ በርግጥ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ድርሻቸውን ርስት አድርገህ ልትሰጣቸው ስለሚገባ የአባታቸውን ድርሻ ለእነርሱ አስተላልፍላቸው።
ከዚህ በኋላ ሙሴ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “የዮሴፍ ነገድ የተናገረው ትክክል ነው፤
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የተናገሩት መልካም ነው፤
አንተ ቅረብ፤ አምላካችን እግዚአብሔር የሚለውን ሁሉ ስሙ፤ ከዚያም አምላካችን እግዚአብሔር የሚነግርህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንሰማለን፤ እናደርገዋለንም።”