ይኸውም የቈየ ጠላትነት ሳይኖር፣ በድንገት ባልንጀራውን የገደለ ማንኛውም ሰው ሸሽቶ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመሄድ ሕይወቱን ማትረፍ ይችል ዘንድ ነው።
“ለሌዋውያኑ ከምትሰጧቸው ከተሞች ስድስቱ፣ ሰው የገደለ ሸሽቶ የሚጠጋባቸው መማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞች ስጧቸው፤
በዚያ ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ፤
ከተሞቹም በምድረ በዳው በከፍተኛ ቦታ ላይ የምትገኘው ቦሶር ለሮቤላውያን፣ በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ለጋዳውያን፣ በባሳን ያለችው ጎላን ለምናሴያውያን ነበሩ።
እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።