ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ፤ የአለቃም ድርሻ ለርሱ ተጠብቆለታል። የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፈቃድና፣ በእስራኤል ላይ የበየነውን ፍርዱን ፈጸመ።”
የሮቤል ነገድ ቤተ ሰቦች፣ የጋድ ነገድ ቤተ ሰቦች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ተቀብለዋልና።
ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ እንዲሁም ከብቶቻችሁ ሙሴ በሰጣችሁ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ባለው ምድር ይቈዩ፤ ነገር ግን ተዋጊዎቻችሁ ሁሉ፣ ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ ከወንድሞቻችሁ ቀድመው ይሻገሩ፤ እናንተም ከወንድሞቻችሁ ጐን ተሰለፉ።
የዝማሬ ድምፅ ስሙ። ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል። “ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ።
“በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣ ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ።