እጄን ወደ ሰማይ አነሣለሁ፤ ለዘላለምም ሕያው እንደ ሆንሁ እናገራለሁ፤
አብራም ግን ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ሰማይንና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ ልዑል አምላክ እጆቼን አንሥቻለሁ፤
አብርሃምም በቤርሳቤህ የተምር ዛፍ ተከለ፤ በዚያም እግዚአብሔር የዘላለም አምላክን ስም ጠራ።
“እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን! አምላኬ የድነቴ ዐለት ከፍ ከፍ ይበል።
አንደበታቸው ሐሰትን ከሚናገር፣ ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው፣ ከባዕዳን እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም።
አንደበታቸው ሐሰትን ይናገራል፤ ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት።
ከዚያም ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅ፣ ለያዕቆብ እሰጣችኋለሁ ብዬ ወደ ማልሁላቸው ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”
በእውነት፣ በቅንነትና በጽድቅ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብለህ ብትምል፣ አሕዛብ በርሱ ይባረካሉ፤ በርሱም ይከበራሉ።”
በግብጽ የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛውም የግብጽ ክፍል የሚኖር ማንኛውም አይሁዳዊ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን!” ብሎ ስሜን እንዳይጠራ፣ እንዳይምልም በታላቁ ስሜ ምያለሁ፤
እንዲህም በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እስራኤልን በመረጥሁበት ቀን፣ ለያዕቆብ ቤት ዘር እጄን አንሥቼ ማልሁላቸው፤ በግብጽም ራሴን ገለጥሁላቸው። እጄንም አንሥቼ፣ “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ አልኋቸው።”
በዚያ ቀን፣ ከግብጽ አውጥቻቸው ከምድር ሁሉ ይልቅ ውብ ወደሆነችው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወዳዘጋጀሁላቸውም ምድር እንደማስገባቸው ማልሁላቸው።
ጻድቁንም ክፉውንም ስለማስወግድ ሰይፌ ከደቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ባለው ሕዝብ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል።
ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝሁት እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ሕዝቡ ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም ወደ ሰገባው አይመለስም።’
ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረው በፍታ የለበሰው ሰው፣ ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፣ “ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመንም እኩሌታ ይሆናል፤ የተቀደሰው ሕዝብ ኀይል መሰበር ሲያከትም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይፈጸማሉ” ብሎ ለዘላለም በሚኖረው በርሱ ሲምል ሰማሁ።
ይሁን እንጂ ሕያው እንደ መሆኔና የእግዚአብሔርም ክብር ምድርን ሁሉ የሞላ እንደ መሆኑ መጠን፣
ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ይሰግዱ ነበር፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው እንዲህ ይላሉ፤
ሕያዋን ፍጡራኑ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ክብር፣ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፣