እንዲህም ይላል፤ “መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፣ እነዚያ አማልክታቸው የት አሉ?
አምላኬ፣ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፤ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ ከዐመፀኛ ሰዎችም ታድነኛለህ።
ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፤ “ከአንተ ጋራ ምን የሚያገናኘን ጕዳይ አለና መጣህ፤ አሁን የአባትህና የእናትህ ነቢያት ወዳሉበት ሂድ” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፣ “ይህማ አይሆንም፤ በሞዓብ እጅ አሳልፎ ሊሰጠን እኛን ሦስት ነገሥታት አንድ ላይ የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ።
“በምድሪቱ ከሚኖሩት ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና መሥዋዕትም ባቀረቡላቸው ጊዜ ይጋብዙሃል፤ አንተም መሥዋዕታቸውን ትበላለህ።
ጠንካራ ምሽጉ በሽብር ምክንያት ይወድቃል፤ መሪዎቹም የጦር ዐርማ ሲያዩ በድንጋጤ ይዋጣሉ” ይላል እሳቱ በጽዮን፣ ማንደጃውም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።
የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ሄደው ይጮኻሉ፤ እነርሱ ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ ሊረዷቸው አይችሉም።
ታዲያ፣ ልታመልካቸው ያበጀሃቸው አማልክት ወዴት ናቸው? በመከራህ ጊዜ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ፣ ይሁዳ ሆይ፤ እስኪ ይምጡና ያድኑህ፤ የከተሞችህን ቍጥር ያህል፣ የአማልክትህም ብዛት እንዲሁ ነውና።
ለመሆኑ፣ ‘የባቢሎን ንጉሥ እናንተንም ይህችንም ምድር አይወጋም’ ብለው ትንቢት ይናገሩ የነበሩት ነቢያታችሁ ወዴት ናቸው?
ሂዱና ወደ መረጣችኋቸው አማልክት ጩኹ፤ መከራ በሚያገኛችሁ ጊዜ እስኪ ያድኗችሁ።”