Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘዳግም 28:57

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከማሕፀኗ የወጣውን እንግዴ ልጇንና የምትወልዳቸውን ሕፃናት ትጠየፋለች፤ ይህን የምታደርገውም በመከራው ወቅት ጠላቶችህ ከተሞችህን ከብበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፣ እነርሱን ደብቃ ለመብላት ስትል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤ የገዢነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል። ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል።

ከዚያም፣ “ለመሆኑ ችግርሽ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት፤ “ይህች ሴት፣ ‘ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪው፤ ነገ ደግሞ የእኔን ልጅ እንበላዋለን’ አለችኝ።

ስለዚህ ልጄን ቀቅለን በላነው። በማግስቱም፣ ‘እንድንበላው ልጅሽን አምጪው’ አልኋት፤ እርሷ ግን ደበቀችው።”

“እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም!

ሕዝቤ ባለቀበት ጊዜ፣ ምግብ እንዲሆኗቸው፣ ርኅሩኆቹ ሴቶች በገዛ እጆቻቸው፣ ልጆቻቸውን ቀቀሉ።

ጠላቶችህ ከብበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፣ ከሥቃይ የተነሣ፣ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን፣ የወገብህ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች