“ከዐማቱ ጋራ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።
“ ‘ከእናቲቱና ከሴት ልጇ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እነርሱ የሥጋ ዘመዶቿ ናቸው፤ ይህም ጸያፍ ነው።
“ ‘አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቷን ቢያገባ፣ አድራጎቱ ጸያፍ ነው፤ በመካከላችሁ እንዲህ ዐይነት ርኩሰት እንዳይገኝ ሰውየውና ሴቶቹ በእሳት ይቃጠሉ።
“በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።