ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷልና አንድ መቶ ሰቅል ብር ያስከፍሉት፤ ገንዘቡንም ለልጅቱ አባት ይስጡት፤ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።
“በጥል ላይ ያሉ ሰዎች ነፍሰ ጡር ሴት ቢመቱና እርሷም ያለጊዜዋ ብትወልድ፣ ጕዳቱም ለክፉ የማይሰጥ ቢሆን፣ ጕዳት ያደረሰባት ሰው የሴትየዋ ባል የጠየቀውንና ፈራጆቹ የፈቀዱትን ካሣ ሁሉ መክፈል አለበት።
ከዚያም በኋላ የከተማው አለቆቹ ሰውየውን ይዘው ይቅጡት፤
ሆኖም ክሱ እውነት ሆኖ ሴቲቱ ድንግል ለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ ማቅረብ ካልተቻለ፣
ሰውየው ለልጅቱ አባት ዐምሳ ሰቅል ብር ይክፈል፤ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሯታልና፣ እርሷን ማግባት አለበት፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።