ሱፍና በፍታ አንድ ላይ ተፈትሎ የተሠራ ልብስ አትልበስ።
“ ‘ሥርዐቴን ጠብቁ። “ ‘የተለያዩ እንስሳትን አታዳቅል። “ ‘በዕርሻህ ላይ ሁለት ዐይነት ዘር አትዝራ። “ ‘ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።
ደግሞም እንዲህ ሲል ምሳሌ ነገራቸው፤ “ከአዲስ ልብስ ላይ ቍራጭ ጨርቅ ቀድዶ በአሮጌ ልብስ ላይ የሚጥፍ ማንም የለም፤ እንዲህ ቢደረግ አዲሱ ልብስ ይቦጨቃል፤ አዲሱም ዕራፊ ለአሮጌው ልብስ አይስማማውም።
በምትለብሰው ልብስ ላይ በአራቱ ማእዘኖች ዘርፍ አድርግ።